Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጠላትን በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን – ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ተናገሩ፡፡

በኢፌዴሪ አየር ኃይል የሰራዊት ቤተሰብ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች የተከበረ ሲሆን ፥ የሰራዊት አባላትና ቤተሰቦቻቸው የአየር ኃይልን የዝግጁነት አቅምና በተቋሙ ውስጥ እየተሰሩ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችን ጎብኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ የተገኙት የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ እንዳሉት ፥ ወታደር የቤተሰብ ድጋፍ ሲኖር ይጀግናል ፤ ለድልም ይበቃል ፤ ለቀጣይ ግዳጅም መነሳሳትን ይፈጥራል።

አክለውም ፥ ‘’አየር ኃይላችን ላስመዘገበው ውጤታማ የግዳጅ አፈፃፀም ስኬት የእናንተ የቤተሰቦቻችን ድርሻ የላቀ በመሆኑ ልትኮሩም ፤ ልትመሰገኑም ይገባችኋል’’ ነው ያሉት።

“እኛ የአየር ኃይል አባላቶች ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ መስራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

በቀጣይም የሰራዊቱንና የቤተሰቦቹን ኑሮ ለመደጎም በትኩረት እንደሚሰራ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version