አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከደቡብ ኮሪያ ውኃ ኮርፖሬሽን ጋር የትብብር ስምምነት በደቡብ ኮሪያ፣ ሲዎል ተፈራርሟል።
የደቡብ ኮሪያ ውኃ ኮርፖሬሽን ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ፓርክ ጄይ ስምምነቱን ከተፈራረሙ በኋላ ባደረጉት ትግግር ÷ የኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ግንኙነት እንደማንኛውም ሀገር የዲፕሎማሲና የልማት ትብብር ብቻ ሳይሆን በደም የታተመ መሆኑን አንስተው ኮርፖሬሽኑ ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሐብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው፥ ከድርጅቱ ጋር በውኃና ኢነርጂ ዘርፍ በቀጣይነት መሥራት እንደሚፈልጉ ገልጸውላቸዋል።
የድርጅቱ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ በጥቅምት ወር 2015 ኢትዮጵያን እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ሲል መረጃውን ይፋ ያደረገው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

