አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ብሎም በማጃንግ ዞን የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል እና የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት አመራሩ እና ማህበረሰቡ በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ታንኳይ ጆክ ከማጃንግ ብሄረሰብ ዞን የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ በክልሉ ብሎም በማጃንግ ዞን የተገኘውን ሰላም ለማስቀጠል እና የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት አመራሩ እና ማህበረሰቡ በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገልጿል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች÷ ስለ ሜጢ ከተማ አስተዳደር ጉዳይ፣ በከተማው ስላለው የውሀ ግንባታ፣ የመንገድ ግንባታ መጓተት፣ ሕገ ወጥ የደን ጭፍጨፋን መከላከል፣ የተገኘውን ሰላም ከማስቀጠል አኳያና መሰል ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
አቶ ኡሞድ ኡጅሉ በሰጡት ምላሽ÷ በሜጢ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር በመኖሩ ምክንያት የተወሰነ አገልግሎት መስጠት እንዲችል የመጀመሪያ ምዕራፍ ርክክብ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ሕገ ወጥ የመሬት ወረራና የደን ጭፍጨፋን ለመከላከል ማህበረሰቡ ከመንግስት ጎን ሆኖ ደኑን ከጨፍጫፊዎች መታደግ እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል፡፡
የሜጢ ከተማ አስተዳደር ጉዳይን በተመለከተ ሰንሰለቱን ጠብቆ እስከመጣ ድረስ ከተማ አስተዳደር ከመሆን የሚያግደው ጉዳይ ባለመኖሩ የሚሟሉ ነገሮች ተሟልተው በሂደት ይስተካከላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽ ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ታንኳይ ጆክ በበኩላቸው÷ የመንገድ ግንባታዎች እንዲጠናቀቁ ከሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት ጋር እየተነጋገርንበት ነው ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

