Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዶክተር ሊያ ታደሰ ከሮታሪ ክለብ ኢትዮጵያ የፀረ ልጅነት ልምሻ ኮሚቴ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ከሮታሪ ክለብ ኢትዮጵያ የፀረ ልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ኮሚቴ ሊቀመንበር ትዕግስት ይልማ እና አንድሬው ስቴይን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም በአፍሪካ እና ዓለም ላይ አዳዲስ እየተከሰተ ባለው የልጅነት ልምሻ ላይ ትኩረት አድርገው መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
በዚህ ወቅትም የልጅነት ልምሻን ለመቆጣጠር እና ክትባቱን ለማስፋፋት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰራውን ስራ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም በልጅነት ልምሻ ተጠቂ ለሆኑ ዜጎች እንዲሁም ኢትዮጵያ የልጅነት ልምሻን ለማጥፋት ለምታደርገው ጥረት መደረግ ባለባቸው ተጨማሪ ድጋፎች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን ነው ያስታወቁት።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version