አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ወርቅ ሲሰርቁ የነበሩ የውጪ ዜጎች መያዛቸውን ማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ ።
የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በሰጡት መግለጫ ለሁለት ሳምንት በተደረገ ዘመቻ ወንጀለኞቹ መያዛቸውን ተናግረዋል ።
በኦሮሚያ ፣ ቤኒሻንጉል እና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች በህገ ወጥ መንገድ ወርቅ ሲያወጡና ሲያዘዋውሩ የተገኙ ተጠርጣሪዎችን ተይዘው እየተጣራ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።
ከኢትዮጵያ ዜጎች ጋር በመተባበር ህገ ወጥ ድርጊቱ ላይ የተሳተፉት በብዛት ቻይናውያን መሆናቸውም ተገልጿል።
ያለጥፋታቸው የታሰሩ ካሉም ተጣርቶ እንደሚለቀቁ ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል።
በምንተስኖት ሙሉጌታ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

