Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በበዓላት ወቅት የሃሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበዓላት ወቅት ከሚፈፀም ግብይት ጋር ተያይዞ ሊያጋጥም የሚችል የሃሰተኛ ገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 396 ባለ ሁለት መቶ ሃሰተኛ የብር ኖት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሦስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ሃሰተኛ ገንዘቡን ይዘው ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር የዋሉት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 15 ልዩ ቦታው ኦሮሚያ ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ፖሊስ እንዳስታወቀው ፥ ግለሰቦቹ ባጃጅ ተሳፍረው ለመጓዝ በእንቅስቃሴ ላይ እያሉ ህብረተሰቡ በተመለከተው አጠራጣሪ ጉዳይና ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተደረገ ፍተሻ 396 ሃሰተኛ ባለ ሁለት መቶ የብር ኖቶችን ይዘው ተገኝተዋል።

በበዓላት ወቅት የሚኖረውን ግብይት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሃሰተኛ የብር ኖቶችን ለማዘዋወር እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ግለሰቦች ስለሚያጋጥሙ ነጋዴውም ሆነ ሸማቹ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲገጥሙት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version