አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መጪውን በዓል ምክንያት በማድረግ ለበዓል ፍጆታ የሚሆኑ ምርቶች ወደ አዲስ አበባ ከተማ እየገቡ መሆኑን ከተማ አስተዳደሩ ገልጿል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ መጪውን ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ ለበዓል ፍጆታ የሚሆኑ በርካታ ምርቶች ወደ ከተማዋ እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ምርቶቹ በተለያዩ የእሁድ ገበያና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች እንደሚገኙ ጠቅሰዋል፡፡
የእሁድ ገበያ ከእሁድ ቀን በተጨማሪ እስከ አዲስ አመት ድረስ የሚዘልቅ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ህብረተሰቡ ያለ አግባብ ዋጋ ከሚጨምሩና የኢኮኖሚ አሻጥር ከሚፈጥሩ አካላት ራሱን በመጠበቅ በየአካባቢው በሚገኝ የእሁድ ገበያና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች እንዲገበያይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

