Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዲስ አበባ ቤት ለቤት የሚደረግ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እንደሌለ የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመዲናዋ ቤት ለቤት የሚደረግ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እንደሌለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤት ላይ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ እንደሚገኝም የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

ሆኖም ግን ይህንን ሽፋን በማድረግም መድሀኒት እንረጫለን በማለት የዘረፋ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ስለመሆኑ መረጃዎች እየደረሱን ይገኛሉ ብሏል።

ስለሆነም የመድሀኒት ርጭቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መኖሪያ ቤትና የተገለገሉባቸው ቁሳቁሶች ብቻ ላይ የሚደረግ መሆኑን ነው የከተማ አስተዳደሩ ያስታወቀው።

ከዚያ ውጪ ምንም አይነት የመድሀኒት ርጭት እየተካሄደ አለመሆኑ ታውቆ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

Exit mobile version