Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሸባሪው ህወሓት በአንድ ቤት ውስጥ 10 ንጹሃን ዜጎችን በግፍ ገደለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአንድ ቤት ውስጥ 10 ንጹሃን ዜጎችን በጭካኔ መግደሉ ተገለጸ፡፡
አሸባሪ ቡድኑ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰቆጣ ወረዳ ልዩ ስሙ ወለህ በሚባል አከባቢ 10 ንጹሃን ዜጎችን በግፍ መጨፍጨፉን የዞኑ አስተዳደር ገልጿል፡፡
ወ/ሮ ለምለም አዳነ የወለህ ማርያም ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። ልጆቻቸውን ለማሳደግ፣ ለማስተማርና ለቁም ነገር ለማድረስ ደፋቀና እያሉ በነበሩበት ስዓት በጭካኔ የተሞላው እና ለንጹሃን የማይራራው የሽብር ቡደኑ ከነ ልጆቻቸው በጭካኔ ገድሏቸዋል፡፡
ከተገደሉት ንጹሃን ዜጎች መካከል ሰባቱ ወ/ሮ ለምለም አዳነ እና 6 ልጆቻቸው ሲሆኑ፥ ሌሎቹ 3ቱ ደግሞ ተፈናቃዮች መሆናቸው ታውቋል።
የሰላም ድርድሩን ወደጎን በማለት ድጋሜ ነፍጥ ያነሳው የሽብር ቡድኑ ህወሓት ነፍጥ ሰላማዊ የሆኑና ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሴትና ሕፃናንትን በከባድ መሳሪያ መጨፍጭፎ መግደሉ ነው የተገለጸው ።
ይህ የአሸባሪ ቡድኑ የጭካኔ ድርጊት፥ ከሰላም ይልቅ ለጦርነት እጁን የዘረጋ፣ የሀገሪቱ ዜጎች በሰላም እንዳይኖሩ የወጠነ ጨፍጫፊ ቡድን መሆኑን ያሳየበት ነው መባሉን ከዋግኸምራ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version