Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሊዝ ትረስ ቀጣይ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዝ ትረስ አዲሷ ቀጣይ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተረጋገጠ።

በሀገሪቱ ፓርላማ አብላጫ መቀመጫ ያለው ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪ አድርጎ መምረጡን ተከትሎ ነው ቀጣይዋ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው የተረጋገጠው።

ትረስ ተፎካካሪያቸው የሆኑትን ሪሺ ሱናክን በማሸነፍ መመረጣቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።

በምርጫው ትረስ 81 ሺህ 326 ድምጽ ሲያገኙ፥ ሪሺ ሱናክ ደግሞ 60 ሺህ 339 ድምጽ አግኝተዋል ነው የተባለው።

ዕጩዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ትረስ፥ የፖለቲካውን ዓለም ከመቀላቀላቸው በፊት የሂሳብ አያያዝ እና የኢኮኖሚ ባለሙያ ሆነው ሰርተዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የፓርላማ አባል ሆነው የተመረጡት ደግሞ በፈረንጆቹ 2010 መሆኑ ታውቋል።

የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ምክትል የገንዘብ ሚኒስትር እና የግምጃ ቤት ሚኒስትር በመሆንም በተለያዩ የመንግስት የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል።

ሊዝ ትረስ ፥ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች እናት መሆናቸውም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version