Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሱዳን የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 112 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከግንቦት ወር ጀምሮ በሱዳን በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 112 ደረሠ።

ባለፈው ሳምንት ብቻ በሀገሪቱ የጎርፍ አደጋ የ12 ሰዎች ህይወት ማለፉን ባለስልጣን ተናግረዋል።

ቢያንስ 115 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ነው የተመለከተው።

በዚህ አመት ከመደበኛው ጊዜ ቀደም ብሎ የጀመረው ዝናብ 85 ሺህ የሚጠጉ ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን፣ ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎች የመንግስት ተቋማትን አጥለቅልቋል።

ከሟቾቹ መካከል 74 ሰዎች በውሃ ውስጥ ሰጥመው፣ 32 ሰዎች ደግሞ ቤታቸው በላያቸው በመፍረስ እና 6 ሰዎች በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወታቸው ማለፉን ተጠቁሟል።

የሱዳን የዝናብ ወቅት አብዛኛውን ጊዜ በሰኔ ወር የሚጀምር እና እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ የሚቆይ ሲሆን በነሀሴ እና መስከረም ላይ ከፍ ያለ ጎርፍ እንደሚያስከትል ይጠበቃል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው በሱዳን ከሚገኙት 18 ግዛቶች በ15ቱ ቢያንስ 258 ሺህ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ተጎድተዋል።

ምንጭ፡- አፍሪካ ኒውስ

Exit mobile version