አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 9ኛው ዓለም አቀፍ የፖሊሲ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ጉባኤው በአየር ንብረት ለውጥ ፣በአፍሪካ የሕፃናት መብቶች እና ተጠያቂነት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነው እየተካሄደ ያለው።
ጉባኤው በአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽፅዕኖን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በሚያስፈልጉ የገንዘብ ምንጮች እና ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን አስፈላጊነት ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል።
ተሳታፊዎቹ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የህጻናት መብት ባለሙያዎች እና የሲቪክ ማህበራት ድርጅት የተውጣጡ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በጉባዔው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንዳሉት ፥ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ሳቢያ የአፍሪካ ህፃናት መብት ጥበቃ፣ ጤና እና ትምህርት የማግኘት መብት ተጥሷል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

