Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሊዝ ትረስ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ47 ዓመቷ ሊዝ ትረስ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በንግሥት ኤልዛቤት ተሾሙ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን ከሥልጣን መልቀቅ ተከትሎ፥ እሳቸውን ለመተካት በወግ አጥባቂ ፓርቲው ውስጥ በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ አብላጫ ድምጽ ያገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሊዝ ትረስ ትናንት የወግ አጥባቂው ፓርቲ መሪ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

ሊዝ ትረስ በስድስት ዓመታት ውስጥ የአገሪቱ ወግ አጥባቂ ፓርቲ ሦስተኛዋ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተገልጿል።

የ96 ዓመቷ ንግሥት ኤልዛቤት፥ ሊዝ ትረስን ተቀብለው ያነጋገሯቸውና የመንግስት አስተዳደራቸውን እንዲመሰርቱ ትዕዛዝ መስጠታቸውንም ሬውተርስ ዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትሯ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ለመላው የብሪታንያ ሕዝብ ንግግር እንደሚያደርጉና ካቢኒያቸውንም ይፋ ማድረግ እንደሚጀምሩ ይጠበቃል ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ባደረጉት የስንብት ንግግር፥ ተግባራቸውን እንዳጠናቀቁ ገልጸው፥ የፓርቱው አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ተረስ ጎን በአንድነት እንዲቆሙ ጠይቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version