Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአዘዞ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 308 ሽጉጥ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 308 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ተያዘ።
 
የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ሳጅን ደመቀ ዘለቀ÷ህገ ወጥ ሽጉጡ በድማዛ ቀበሌ አጣጥ ተብሎ በሚጠራው ኬላ በተደረገ ፍተሻ ነው የተያዘው፡፡
 
ህገ ወጥ ሽጉጡ ከመነሻው ጀምሮ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፍተኛ ክትትል ሲደረግበት እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
 
ህገ ወጥ ሽጉጡን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑንም ከክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version