አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ከቶኒ ብሌር ኢንስቲትዩት መስራች፣ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የታላቋ ብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ዶክተር በለጠ ኢንስቲትዩቱ በተለይም በዲጂታል መንግሥት፣ በዲጂታል ግብይትና መታወቂያ፣ በዲጂታል መሰረተ ልማትና መሰል ሥራዎች ላይ እያደረገ ያለውን ድጋፍ ማድነቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የዲጂታል ዕውቀትን በማስፋፋት ረገድና በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂው የተለዩትን ፕሮጀክቶች ለመፈፀም የሚያስችል የአቅም ግንባታና የባለሙያ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።
ቶኒ ብሌር በበኩላቸው÷ ኢንስቲትዩቱ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ በማጠናከር የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ጉዞ ለማገዝ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡
በዲጂታል አገልግሎት፣ በዲጂታል መሰረተ ልማት፣ በዲጂታል ፖሊሲና አፈፃፀምን ለመለካት በሚያስችሉ ሥራዎች ላይ በጋራ እንሠራለን ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

