Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ ከኮሮናቫይረስ ነጻ መሆናቸው ታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮናቫይረስ ከተያዘው ጃፓናዊ ጋር ንክኪ የነበራቸው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገለጸ።

ከ12 ቀናት በፊት ከጃፓናዊው ጋር ንኪኪ የነበራቸው  21 ሰዎች ነጻ መሆናቸውን በሐኪሞች እንደተገለጸላቸው ዶክተር ቶላ ተናግረዋል።

በጃፓናዊው ላይ ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘ ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ ለብቻቸው ተቀምጠው የነበሩት ዶክተር ቶላ በተደረገላቸው ምርምራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዘው ጃፓናዊ ከእሳቸው በተጨማሪ በአርሲ ዞን ሁለት ትምህርት ቤቶችን ሲጎበኙ ንኪኪ አላቸው የተባሉት ሁሉም ሰዎች ነጻ መሆናቸው ታውቋል።

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 5 ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ ያላቸው 992 ሰዎች ባሉበት ቦታ ለ14 ቀናት የጤና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Exit mobile version