አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስቶች ጳጉሜን 5 ቀን ለሚከበረው የአንድነት ቀን “ስናብር ስናምር የተሰኘ” የሙዚቃ ክሊፕ ሰርተው አስረከቡ፡፡
አርቲስቶቹ ስለ አንድነት፣ ሰላም፣ ፍቅር እና መተሳሰብ የሚሰብኩ የሙዚቃ ስራዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርተው በማጠናቀቅ የአንድነት ቀን አዘጋጅ ኮሚቴዎች በተገኙበት ለመከላከያ ሚኒስተር ዶክተር አብርሃም በላይ አስረክበዋል፡፡
የሙዚቃ ክሊፑ አምስት የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን (ቪዲዮዎችን) የያዘ ሲሆን፥ ስራዎቹ ብዝሃነትን በሚያንጸባርቅ መልኩ የተሰሩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የሙዚቃ ክሊፑ ስራ ላይ ስመ ጥር ባለሙያዎች የተሳተፉበትና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተሰራ መሆኑም ተገልጿል።
በመራኦል ከድር
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

