አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አዲስ አመትን ከአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ጋር በታላቁ ቤተመንግሥት አከበሩ።
ከልደታ፣ ቂርቆስ እና አራዳ ከፍለ ከተሞች ለተውጣጡ አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማዕድ ተቋድሰዋል፤ የበዓል ስጦታም አበርክተዋል ።
አረጋውያኑ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
አዲሱ አመት የሰላም እና የስኬት እንዲሆንም ነው የተመኙት።
በአልአዛር ታደለ

