አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በያዝነው ዓመት ስምንት የማስተላለፊያ መስመርና የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ግንባታ ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚ ክብሮም ካህሳይ እንደገለጹት÷ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት በውጪ ሥራ ተቋራጮችና በተቋሙ የራስ ኃይል ኮንስትራክሽን መምሪያ ይከናወናል፡፡
የበቆጂ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት፣ የደብረ ታቦር ባለ 230/33/15 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ እና በአዳማ ከተማ ለሚገነባው ገዳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ኃይል ለማቅረብ የሚገነባው የማከፋፈያ ጣቢያ በተቋሙ የራስ ኃይል መምሪያ እንደሚገነቡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መረጃ አመላክቷል፡፡
የደቡባዊ ኤሌክትሪክሲቲ ግሪድ የማስፋፊያ ፕሮጀክት እና የቡታጅራ – ወራቤ የማስተላለፊያ መስመርና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች በውጭ ሥራ ተቋራጮች እንደሚገነቡም ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

