አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ-መሓላ ፈፀሙ።
በበዓለ ሲመቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሩቶ ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ከ50 በመቶ በላይ የሆነውን የመራጮች ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡
ከ14 ሚሊየን በላይ ኬንያውያን ድምጽ የሰጡበት የኬንያ ምርጫ፥ አራት ዕጩዎች ተፎካክረውበታል።

