አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልሎች እና የተለያዩ ተቋማት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተለያዩ ድጋፎችን አደረጉ።
ድጋፎቹ የጥሬ ገንዘብ፣ የሰንጋ እና የአይነት ድጋፎች ናቸው።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እና የነዳጅ አቅራቢ ድርጅቶች ናቸው ድጋፉን ያደረጉት።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች 26 ሚሊየን ብር እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት 90 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
የነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ደግሞ 2 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ለግሷል።
የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው መሰል ድጋፎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ጠይቀዋል።
በተመሳሳይ የብሔራዊ ባንክ አመራሮች እና ሠራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉም 19 ሚሊየን ብር መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡
በወንድሙ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!