አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት፣ የሸካ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የስደተኞች እና ተመላሾች አገልግሎት በዛሬው ዕለት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአምስት ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በተመሳሳይ የሸካ ዞን ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ3 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሰንጋዎች፣ በግ እና ፍየሎች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋ አድርጓል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞንም ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሰንጋዎች፣ በግ እና ፍየሎች ለ2ኛ ዙር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ዞኖቹ የአሸባሪው ህወሓት አከርካሪ ተመቶ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እስኪረጋገጥ ድረስ ለመከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ደጀንነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

