Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብሔራዊ የመታወቂያ ቀን እና ዲጅታል መታወቂያ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ የመታወቂያ ቀን እና የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሄደ፡፡

 

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ፥ ብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ የዜጎችን ደኅንነት ለመጠበቅ ያስችላል ብለዋል።

 

ከዚህ ባለፈም ዜጎች ከመንግሥት የሚያገኙትን አገልግሎት በፍትሃዊነት እንዲያገኙ እና የተለያዩ ወንጀሎችን በተለይ የሳይበርና ሌሎች የማጭበርበር ወንጀሎችን ለመቀነስ አስቻይ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

 

መረጃዎች በተገቢው ተመስጥረው እና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ብሎም በቅርቡ ቁልፍ የህዝብ መሰረተ ልማትን ወደ ትግበራ ለማስገባት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

 

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ዬዳሄ አርአያስላሴ በበኩላቸው፥ የብሔራዊ መታወቂያ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ፋይዳውን ሁሉም ዜጋ በመረዳት በፍቃደኝነት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

 

የሚመለከታቸው መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ እና የግሉ ሴክተር ተቋማትም የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምን እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

 

በመርሐ ግብሩ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም አጋር ድርጅቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል።

 

Exit mobile version