አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በነቀምቴ ከተማ በሶርጋ ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
በሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን በነቀምቴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስቴክተር ይገዙ ዲሳሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
አደጋው የደረሰው ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ ፍሬን በመበጠሱ ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በገላና ተስፋ

