Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ የፊታችን ሰኞ መደበኛ ትምህርት ይጀመራል

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በመጪው ሰኞ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ትምህርት ለማስጀመር የተደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

 

በመግለጫቸውም በትምህርት ዘመኑ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር የሚያስችል ስርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡

 

ትምህርት ቤቶችን ለተማሪዎችና ለመምህራን ምቹ ከማድረግ ጀምሮ አስፈላጊ የተባሉ ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የቢሮ ሃላፊው በመግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡

 

የፊታችን መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት በመዲናዋ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ይጀመራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version