አዲስ አበባ ፣ መስከረም 10 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎችን አሳፍሮ መነሻውን ከመካነሰላም በማድረግ ወደ ግሸን ደብረከርቤ ሲያመራ የነበረ ሲኖትራክ የጭነት መኪና ተገልብጦ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው ለጋምቦ ወረዳ 029 ቀበሌ ልዩ ቦታው እህል ማፍሰሻ ከተባለው ስፍራ ከማለዳው 12:00 ሰዓት ላይ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ በመገልበጡ መድረሱ ተገልጿል።
በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ በ15 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የወረዳው ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን ተጎጅዎችን ወደ ሆስፒታል እንዲደርሱ ማድረጉን የቦረና ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!