አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን እየታደገ የሚገኘውን የከተሞች ሴፍቲኔት ልማት ፕሮጀክት ለማሳደግ የሚያግዙ ተሽከርካሪዎችን ለተጠቃሚ ከተሞች አስረከበ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፥ ለ67 ከተሞች 72 ለሁለገብ ስራ የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎችን ሚኒስቴሩ አስረክቧል።
በተጨማሪም 144 ሞተር ሳይክሎች ተከፋፍለዋል።
ተሽከርካሪዎቹ እና ሞተሮቹ ከተሞ የሴፍቲኔት ልማት ፕሮጀክቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በእጅጉ የሚያግዙ መሆናቸውን ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
“በቀጣይም የዜጎችን ህይወት በተጨባጭ እየለወጠ የሚገኘውን ይህን ፕሮጀክት ውጤታማነት ለማረጋገጥ ድጋፉ ይቀጥላል” ብለዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

