Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ 200 ትምህርት ቤቶችን ዘንድሮ መልሶ ለመገንባት እንዳቀደ ሚኒስቴሩ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህውሓት ከወደሙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በዚህ ዓመት 200 ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

 

የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ መልሶ ግንባታ ከሚደረግላቸው 200 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአምስቱ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ተጀምሯል።

 

የተለያዩ ተቋማትም በትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ ላይ ተሳትፎ እያደረጉ ነው ብለዋል።

 

ለትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ሁሉም የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋም ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ትምህርት ቤቶቻቸው በወደሙባቸው አካባቢዎች፥ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ትምህርታቸውን የሚከታተሉባቸው አማራጮች እንደተዘጋጁም ተገልጿል።

 

በዙፋን ካሳሁን

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

 

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version