አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማእድን ሚኒስቴር የተፈጥሮ ጋዝና ነዳጅ የማፈላለግ ስራ ላይ ከተሰማራው ፖሊ ጂ ሲ ኤ ል ከተሰኘው ኩባንያ ጋር የገባውን ውል አቋረጠ።
የማእድን ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከኩባንያው ጋር የነበረው ውል ከትናንት ጀምሮ ተቋርጧል ብለዋል።
ድርጅቱ አስፈላጊው ድጋፍ በመንግስት እየተደረገለት ቢቆይም የፋይናንስና የቴክኒክ አቅም ውስንነት አጋጥሞት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው እንደቆየ አስታውሰዋል።
ባለፉት 10 አመታት ፍለጋ እና ልማት ስራ በማካሄድ ላይ የቆየው ኩባንያው የሚፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ውሉ እንዲቋፈጥ መደረጉን አብራርተዋል።
መሰል እርምጃዎች ለሌሎች ኩባንያዎችም ትምህርት እንደሚሆን እና ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት በአግባቡ መጠቀም ላይ ትኩረት መደረጉን ማሳያ ነው ብለዋል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

