አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደብረ ብርሀን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌን ጨምሮ አምስት ባለሙያዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የከተማው ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር ታዬ ወልደጊዮርጊስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከከተማ መሬት ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው።
ከምክትል ከንቲባው አቶ ደስታ አንዳርጌ በተጨማሪም የከተማው የመሬት ልማት ቡድን መሪ አቶ ደምሴ ተፈረደኝ እና አቶ ኃይሉ ሽፈራው እንዲሁም ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
አመራሮቹ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በአላዩ ገረመው

