Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ መላኩ አለበል ከአፍሪካ ልማት ባንክ የምሥራቅ አፍሪካ አመራር ጋር ተወያዩ

አዲስአበባ፣ መስከረም 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከአፍሪካ ልማት ባንክ የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አብዱል ካማራ ጋር ውይይት አድርገዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ከማዘጋጀት ጀምሮ በኮቪድ ወቅት ኤክስፖርትን ለማስቀጠል እና የተቀናጁ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልማት ጋር የተያያዙ ድጋፎች ዙሪያ ላይ ነው የተወያዩት።

በቀጣይም ረቂቅ የኢንዱስትሪ ፖሊሲውን ወደ ስራ ለማስገባት እንዲሁም ፓርኮቹን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስፈልጉ የምርት ሰንሰለት፣ የፋይናንስ እንዲሁም የተለያዩ የማስተዋወቅ ስራዎች ላይ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ባንኩ ለኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ስራዎች መሳለጥ እያደረገ ስላለው ድጋፍ ሚኒስትሩ የምስጋና ምስክር ወረቀት ማበርከታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version