አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 29ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ “ትምህርት ለብዘሀ ባህልና ለሀገር ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ የ2014 የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ እቅድ ዝግጅት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ፥ በመድረኩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ተወማ ፕሬዚዳንት ኢ/ር ጌታቸው ሰጠኝ ፥ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከምንጊዜውም በላቀ ደረጃ የበኩላቸዉን ሚና እንደሚወም ነው የገለጹት፡፡
አክለውም ፥ የትምህርት ልማት ስራውን ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጎን እንደሚቆሙም ነው የተናገሩት፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፥ ለከተማ አስተዳደሩ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጣቸው ያሉ በመሆናቸዉ የከተማ አስተዳደሩን አመስግነዋል፡፡በቀጣይም የከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ጥያቄዎች የሚሰጠዉን ምላሽ አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ጉባዔው በነገ ውሎው በጋራ ለመሰራት ከተለያዩ ተቋማት ጋር የትስስር ሰነድ ፊርማና የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

