አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን በአንድ ቀን 475 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይዎታቸው አለፈ።
በአንድ ቀን የተመዘገበው የሟቾች ቁጥር ቫይረሱ ከተከሰተ ወዲህ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
በሃገሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ወደ 3 ሺህ መጠጋቱም ታውቋል።
በሃገሪቱ በአጠቃላይ 35 ሺህ 713 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ አገግመው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።
ሰሜናዊቷ ሎምባርዲ ከጣልያን ግዛቶች ወረርሽኙ በስፋት እያጠቃት ይገኛል ነው የተባለው።
የቫይረሱ መነሻ ከሆነችው ቻይና ቀጥሎ ከፍተኛ የሞት መጠን ያስመዘገበችው ጣልያን ሆናለች።
ዓለም ላይ በቫይረሱ ሳቢያ ከ218 ሺህ በላይ ሰዎች ሲያዙ ከ8 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታትም ሃገራት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ሲሆን፥ በርካቶች ድንበሮቻቸውን ዘግተዋል።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

