Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማዲንጎ የተዋጣለት ከያኒ ብቻ ሳይሆን ልበቀናና ሀገር ወዳድ ነበር- አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማዲንጎ የተዋጣለት ከያኒ ብቻ ሳይሆን ልበቀናና ሀገር ወዳድ ነበር ሲሉ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ሕልፈተ ሕይወት እጅግ አሳዛኝ ክስተት ነው ብለዋል፡፡

ማዲንጎ የተዋጣለት ከያኒ ብቻ ሳይሆን÷ ልበቀናና ሀገር ወዳድ፣ እንደሰው ሰከን ያለ ሰብዕና የተላበሰ ሰው እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ዛሬ ሕይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version