አዲስ አበባ፣መጋቢት 10፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የንጽህና እቃዎችን ማሰባሰቢያ ማዕከል በመስቀል አደባባይ ተቋቁሟል።
በከተማዋ ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች የተቋቋመው ኮሚቴ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የንጽህና እቃዎችን የማሰባሰብ ስራ ዛሬ በይፋ መጀመሩን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ህብረተሰቡም ከነገ ጀምሮ ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ማንኛውንም የንጽህና እቃ መለገስ እንደሚችል ተገልጿል።
የከተማ አስተዳደሩ የንጽህና እቃዎችን መግዛት ለማይችሉ ወገኖች ህብረተሰቡ አቅሙ በፈቀደው ልክ ድጋፍ በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በሚሰራው ስራ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ጥሪ አቅርቧል።

