Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ከሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ እና ጣሊያን ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ከሩሲያ፣ ቻይና፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ሲንጋፖር፣ ካሜሩን እና ሶማሊያ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላትን ስምምነት ተፈራርማለች፡፡

የትራንስፖት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በካናዳ እየተካሄደ በሚገኘው 41ኛው ከዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ጉባኤ ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት ልዑካን ቡድኖች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአቪዬሽን ዘርፍ ከሀገራቱ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ወይዘሮ ዳግማዊት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ከልዑካኑ ቡድኑ ጋር በአቪዬሽን ስልጠና እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስትራቴጂያዊ አጋርነት መመስረት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸውን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version