Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ስማርት ስልኮች ከነተጠርጣሪዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ስማርት ስልኮችን ከሦስት ተጠርጣሪዎች ጋር ይዞ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ፖሊስ በህገ-ወጥ መንገድ  ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ አጠቃላይ ዋጋቸው 10 ሚሊየን 725 ብር የሚገመቱ 715 ስማርት ስልኮችን  ባደረገው ክትትል  ከነተጠርጣሪዎቹ  እጅ  ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል፡፡

ስልኮቹ ከነተጠርጣሪዎቹ በዛሬው ዕለት  በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው በተለምዶ 2 ቁጥር አውቶቡስ ማዞሪያ አካባቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው የተያዙት ፡፡

በተጨማሪም ፒካፕና ዶልፊን ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የስልክ ቻርጀሮችና የጆሮ ማዳማጫዎች መያዛቸው ተመላክቷል፡፡

ከተያዙት ስማርት ስልኮች መካከል 455ቱ በፒካፕ ተሽከርካሪው የነዳጅ መያዣ ታንከር አካባቢ በተለምዶ ሻግ(መደበቂያ) ተሰርቶ ተደብቆ መገኘቱ ተጠቁሟል፡፡

ቀሪዎቹን 260 ስማርት ሞባይል ስልኮች ደግሞ ግለሰቦቹ ተከራይተው ከሚኖሩበት ቤት መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ከህግ ተጠያቂነት ነፃ ለመሆን በመፈለግ በቁጥጥር ስር ላዋሏቸው የፖሊስ የክትትል አባላት ስልኮቹን ሁሉ ወስደው እንዲለቋቸውና ተጨማሪ 2 ሚሊየን ብር መደለያ እንዳቀረቡላቸው ተገልጿል፡፡

ሆኖም አባላቱ ሙያዊ ግዴታቸው በብቃት በመወጣት ግለሰቦቹን ህግ ፊት በማቅረብ አኩሪ ተግባር መፈጸማቸውን ከፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version