Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ቀጄላ መርዳሳ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ በኢትዮጵያ ከሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርክሂን ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸውም በቀጣዩ ህዳር ወር በጀርመን ስለሚካሄደውየፓራሊምፒክ ዓለም አቀፍ ኮሚቴ ስብሰባ እና በቀጣይ ሁለቱ ሀገራት በባህል ዘርፍ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ስለሚያደርጉበት ሁኔታ መክረዋል፡፡

በህዳር ወር 2022 በሩሲያ በሚካሄደው የባህል ሚኒስትሮች ጉባዔ እንዲሳተፉ ከሩሲያው አቻቸው የተላከላቸውን ደብዳቤ ከአምባሳደሩ መቀበላቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version