አዲስ አበባ፣መጋቢት 13፣2012(ኤፍ.ቢ፣.ሲ)የሰላም ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ላንበረት መነኻሪያ ተገኝተዉ የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራ አከናውነዋል፡፡
በዚህ ተግባር ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች መገኘታቸው ተገልጿል፡፡
የሚኒስቴሩ አመራሮችና ሰራተኞች ለመንገደኞች እጅ የማስታጠብ ፣ የሳይነተሪ ዕደላ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ማከናወናቸው ነው የተገለጸው፡፡
የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያዊያን ከተባበርንና ተጋግዘን ከሰራን የማንሻገረዉ ችግር፣ የማንፈታዉ ፈተና የለም ብለዋል ።
አያይዘውም አሁን በአገር ደረጃ የተፈጠረዉን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ሁላችንም ትኩረት ሰጥተን ሳንረበሽና ሳንደናገጥ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ ችግሩን ማለፍ እንችላለን ማለታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

