አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ መወሰኑን የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ ተወስኗል።
ውሳኔው በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ብሎም ተማሪዎች በቫይረሱ ምክንያት የከፋ ችግር እንዳይደርስባቸው በማሰብ የተላለፈ መሆኑን ተናግረዋል።
ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱም በትራንስፖርት እጥረት እና መሰል ችግሮች እንዳይስተጓጎሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በመላኩ ገድፍ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision