Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ስለሚኖራቸው ግንኙነት አሠራር ይዘረጋል- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በየአካባቢው የሚገኙ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤቶች በአካባቢያቸው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙነት አሠራር እንደሚዘረጋ ተገለጸ፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የጋሞ ባይራ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ ሞዴል ትምህርት ቤቶች ነገ ሀገሪቱን የሚረከቡ፣ ብልፅግናዋን የሚያፋጥኑ፣ በዕውቀትና በክህሎት የበለፀጉ ዜጎች የሚፈሩባቸው ተቋማት ናቸው።

በየአካባቢው የሚገኙ ሞዴል አዳሪ ትምህርት ቤቶች በአካባቢያቸው ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሊኖራቸው ስለሚገባ ግንኙነት ውይይት በማድረግ አሠራር እንደሚዘረጋም ተናግረዋል፡፡

የጋሞ ባይራ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚቀጥለው ሣምንት የማስተማር ስራ ይጀምራል መባሉን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የጋሞ ባይራ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር እንደሚጀምር እና የመግቢያ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎችም መለየታቸው ተጠቁማል።

 

 

Exit mobile version