Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጎሕ ቤቶች ባንክና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎሕ ቤቶች ባንክ ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አስማረ እና የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ተፈራርመውታል፡፡

ስምምነቱ በተቋማቱ መካከል ያሉ የውክልና፣ የሽያጭና ሌሎች ተጓዳኝ የሰነድ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ በሆነ የኦንላይን አማራጭ ለማከናወን የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያረጋገጣቸውንና የመዘገባቸውን ሰነዶች ባንኩ በቅርንፎቹ መጠቀም የሚችልበት ቀላል አማራጭ በመሆኑ ለተገልጋዮቹ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በጥቅምት ወር 2014 ዓ.ም ስራ የጀመረው ጎሕ ቤቶች ባንክ ከ5 ሺህ 800 በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

 

Exit mobile version