Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በደቡብ ክልል በ679 ሚሊየን ብር የተገነቡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ተቋማት ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ679 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች መመረቃቸውን የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ገለፀ።
ተገንብተው ከተጠናቀቁ ከ12 በላይ ፕሮጀክቶች መካከል በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አንዱ ነው፡፡
የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር እንዳልካቸው ጌታቸው እንደገለፁት÷ ለጠበላ ከተማ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግንባታ ከ61 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡
ኮሌጁ የተገነባው ለጠበላና አጎራባች ወረዳዎች መሆኑን ጠቁመው÷ ስልጠናው እንዲጀመርም አመራሩ በሕዝባዊ ንቅናቄ ግብዓት እንዲሟላ ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን የሰው ኃይል ለማማሟላት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አክሊሉ ለማ፥ በዞኑ ሦስት የኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጆች ተገንብተው መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
በማስተዋል አሰፋ ተጨማሪ መረጃ ከደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version