አዲስ አበባ፣ህዳር 5፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ብሔራዊ የደህንነት አገልግሎት የውጭ ደህንነት ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፍ ሳሊም ሱለይማን የተመራ ልዑክ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝቷል፡፡፡
ልዑካን ቡድኑ በኢመደአ በነበረው ጉብኝት በሳይበር ደህንነት እና ሳይበር ቴክኖሎጂ ልማት ዙሪያ በተቋሙ እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ምርምርና ልማት ሥራዎችን እንዲሁም የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን ተመልክቷል፡፡
በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ያለውን የሰው ሃይል እጥረት ለመቅረፍ ኢመደአ ከታዳጊ ሕጻናት ጀምሮ እየሰራ ያለው ሥራ አበረታች መሆኑን የልዑካን ቡድኑ አባላት ገልፀዋል፡፡
በሰው ሃይል ልማት እንዲሁም በቀጠናዊ የሳይበር ደህንነት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው የሳይበር ደህንነትን ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚደረጉ የጋራ ስምሪቶች ዙሪያ የተለያዩ ምክክሮችን እንደሚያደርግ ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

