አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግኽምራ ዞን ለሚገኙ 42 ሺህ ወገኖች የሚውል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ ማድረጉን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
በዞኑ ዝቋላ ወረዳ፣ ፅፅቃ ከተማ እና አካባቢው ለሚገኙ እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 30 ሺህ ወገኖች የምግብ ድጋፍ መደረጉን የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ልዑክ በኢትዮጵያ መረጃ ያመላክታል፡፡
እንዲሁም ለ12 ሺህ ሰዎች ደግሞ ምግብ ነክ ያልሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

