Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና ኬንያ ሽብርተኝነትና የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ሕዳር 5፣2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና ኬንያ የመረጃና ደኅንነት ተቋማት ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና የተደራጁ ወንጀሎችን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ተስመምተዋል፡፡
 
ስምምነቱን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተመስገን ጥሩነህ እና የኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ፍሊፕ ካሙሩ ተፈራርመውታል።
 
አካባቢያዊ ስጋት የሆኑትን ሽብርተኝነት፣ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች ዝውውርን ፣ ህገ ወጥ የፋይናንስ ዝውውርን ፣ ህገ ወጥ ታጣቂዎችን፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ድንበር ዘለል የተደራጁ ወንጀሎችና ስጋቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የትብብር ስምምነት ሰነድ ውስጥ የተካተቱ ነጥቦች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
 
አቶ ተመስገን በፊርማ ስነ ሥርዓቱ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም እና በአፍሪካ ቀንድ የሽብርተኝነትና ተያያዥ የፀጥታ ችግሮችን በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ስምምነት መፈፀሟን አንስተዋል፡፡
 
በኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት የልዑካን ቡድኑ መሪ ዶ/ር ሰይፍ ሳሌም ሱሌማን በበኩላቸው÷ ሽብርተኝነት፣ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች፣ የገንዘብና የሰዎች ዝውውር ለምስራቅ አፍሪካ ስጋት መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
 
በመሆኑም እነዚህን የቀጠናው ችግሮች ተባበሮና ተቀናጅቶ ለመመከት ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመሥራት ስምምነት ማደረጋቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
የኬንያ ብሄራዊ መረጃ አገልግሎት የልዑካን ቡድን ከትናንት ጀምሮ በኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር፣አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትና ሳይንስ ሙዚየምን እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ተቋማትን ጎብኝቷል።
 
ኢትዮጵያና ኬንያ ወዳጅነት ያላቸው ጎረቤት ሀገራት ሲሆኑ ÷ ለረጅም ጊዜ በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚውና ማህበራዊ ዘርፎች መልካም የሚባል ግንኙነት ያላቸው መሆኑን የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version