Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በአፋር ክልል የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ የሌማት ትሩፋት ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
 
በመርሐ ግብሩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አወል አርባ÷አፋር ክልል የበርካታ ተፈጥሮ ሃብቶች መገኛ አካባቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
በዚህ እምቅ ሃብት ሀገርና ህዝብን ተጠቃሚ ለማድረግም በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።
 
አቶ አወል በአዋሽ ከተማ አካባቢ እየለሙ የሚገኙ የቆላ ስንዴ፣ የእንስሳትና የዶሮ እርባታ እንዲሁም የአሳ ምርቶችን ከክልሉና ከፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
 
አቶ አወል በዚሁ ወቅት÷የዶሮና የአሣ ምርቶችን በተገቢው መንገድ በማምረት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚገባ ተናግረዋል።
 
የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማጠናከር ህብረተሰቡ የተሻለ ገቢ እንዲያገኝ ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉም አሳስበዋል።
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version