አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2024 በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካንን ወክለው በድጋሚ እንደሚወዳደሩ አስታወቁ፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2020 በጆ ባይደን ተሸንፈው በ2021 መንበረ ሥልጣናቸውን በይፋ ማስረከባቸው ይታወሳል፡፡
“አሜሪካን እንደገና ታላቅ እናድርግ” በሚል ንቅናቄያቸው የሚታወሱት የሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ÷ ፍሎሪዳ በሚገኘው ቅንጡ መኖሪያ ቤታቸው ማር-አ-ላጎ ሆነው ነው ለሦስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ይፋ ያደረጉት፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ፍላጎታቸውን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ደጋፊዎቻቸው ቤታቸውን ከበው እንደነበርም ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ÷ የዋሺንግተን ሹማምንት አፋችንን ሊያዘጉ ይፈልጋሉ ፤ እኔ ግን በ2016 ቃል በገባሁላችሁ መሠረት ድምጻችሁ እሆናለሁ ሲሉም ተደምጠዋል ነው የተባለው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

