Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሳዲዮ ማኔ በጉዳት ምክንያት ከዓለም ዋንጫ ውጭ መሆኑ ተረጋገጠ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴኔጋላዊው ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ባጋጠመው ጉዳት ምክንት ከዓለም ዋንጫ ውድድር ውጭ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የቀድሞው የሊቨርፑል ኮከብ ሳዲዮ ማኔ ከጉዳት መልስ በዓለም ዋንጫ በተወሰኑ ጨዋታዎች ላይ ሊደርስ ይችላል  ተብሎ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ  በጉዳት ህጎች መሰረት ተጫዋቹ ከሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ሳዲዮ ማኔ ክለቡ ባየርሙኒክ ከወርደር ብሬመን ጋር ጨዋታውን እያደረገ በነበረበት ወቅት ጉዳት ማስተናገዱ የሚታወስ ነው፡፡

32 ሀገራትን የሚያሳትፈው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከሁለት ቀናት በኋላ በደቡብ ኤስያዋ ሀገር ኳታር የሚጀመር ይሆናል፡፡

 

 

Exit mobile version