Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጣሊያን ለአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ልማት 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚያካሂደው የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚውል 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ ከጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌስ እና ልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የወንዝ ዳርቻ ልማት፣ በመለስተኛ የመጫወቻ ሜዳዎች ልማት እና በባህል ልውውጥ ዙሪያ አብሮ መስራት በሚቻልበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ለአዲስ አበባ ከተማ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ላበረከተው 5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version